የአዘጋጁ መልዕክት፡ ዘ-ሐበሻን እየተፈታተኑ ያሉ ሁኔታዎች


በድጋሚ አሁንም እናስቸግራችሁ!

የተከበራችሁ የዘ-ሐበሻ ድረገጽ ጎብኚዎች!

zehabesha 60 page page 13 to 24በቅድሚያ ዘ-ሐበሻን የወቅታዊ መረጃዎች መገኛ አድርጋችሁ በመምረጣችሁና ሁልጊዜም ስለምትጎበኙን ምስጋናችን የላቀ ነው። ዘ-ሐበሻ ከዕለት ወደ ዕለት ተፈላጊነቷ እየጨመረ መሄዱን በየቀኑ ከምናገኘው ትራፊክ ለመረዳት ችለናል። በዚህም ደግሞ እናንተን ዘ-ሐበሻን ታማኝ የዜና ምንጭ አድርጋችሁ በመምረጣችሁ እናመሰግናችኋለን።

የዓለም አቀፍ የድረገጽ ጎብኚዎችን መረጃ ሰጪ ድርጅት (alexa.com) ዘገባ መሠረት ዘ-ሐበሻ በአሁኑ ወቅት በርካታ ጎብኚዎች ካሉት ድረገጽ መካከል አንዱና አንደኛው ነው።

ዘ-ሐበሻ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘችው በ እናንተ በአንባቢዎቿ ብርቱ ጉብኝት እንደሆነና እኛም 24/7 ድረገጻችንን በወቅታዊ መረጃዎች ማጨቃችን መሆኑ አይተባበልም።

ግን ዘ-ሐበሻ በአሁኑ ወቅት እንደምታቀርበው አገልግሎት ከጎብኚዎቿ የሚገባውን ድጋፍ እያገኘች አይደለችም። ከኢሕአዴግ መንግስት ግን ጡጫዋን እየተቀበለች ቀጥላለች። በተደጋጋሚ እየደረሰብን እንዳለው ባለፉት 24 ሰዓታት ያለን ሰርቨር አንድ ብቻ በመሆኑ ሰርቨራችን መቋቋም ከሚችለው በላይ ጎብኚ ስላለ ድረገጻችን እስከ አገልግሎት አለመስጠት ደርሶ ነበር። በዛ ላይ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከኢትዮቴሎኮም፣ ከጀርመን፣ ከኖርዌይና ከቤልጂየም ተደጋጋሚ ትራፊኮችን በመላክ ድረገጻችን እንዲጨናነቅና ሰዎች እንዳይጎበኙ ለማድረግ የሚያደርገውን የማሰላቸት ተግባር ለመቋቋም ሁለተኛ ሰርቨር እንደሚያስፈልገን ባለፈው ጊዜ ገልጸን ነበር። በሚሊዮን የሚቆጠር የድረገጽ ጎብኚ እያለን ለአንድ ወር የዘ-ሐበሻን የመርጃ ጊዜ ብለን አውጀን ያሰባሰብነው ድጋፍ ለናንተ ለመንገር የሚያሳቅቅ ነው።

ዘ-ሐበሻን በተለያዩ መንገዶች እየረዱ ያሉ ሰዎች አሉ። እነርሱ እንዴት ዘ-ሐበሻን እየረዱ እንዳሉ ጠይቁ። ሆኖም ግን ከ223 ሺህ በላይ የፌስቡክ ተከታይ ያለው ዘ-ሐበሻ፣ በሚሊኖች የሚቆጠር ጎብኚ ያለው ዘ-ሐበሻ ለውጥ እንዲያመጣ የምትፈልጉ ከሆነ ሁለተኛውን ሰርቨር እንድንገዛና የሳይበር ጦርነት የገጠመውን ወያኔን እንድናሸንፍ ልትተባበሩን ይገባል።

እኛ ያለን አቅም ውስን ነው። አቅማችንን እስኪዳከም ድረስ ነፃ፣ ሚዛናዊና፣ ወቅታዊ መረጃዎችን ለሕዝባችን ማድረሳችን አይቀሬ ነው፤ ሆኖም ግን በርቱ የምትሉን ከሆነ በርቱ የምትሉበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባችኋል። ላለፉት 24 ሰዓታት ዘ-ሐበሻ ልትነነበብ ያልቻለችበት ምክንያትም ይኸው ነው።

ዘ-ሐበሻን በገንዘብ ለማገዝ ይኸው ሊንኩ፤

እውነት ያሸንፋል!

Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.
Source Article from http://www.zehabesha.com/amharic/archives/11751

You might like

About the Author: AddisZena

Leave a Reply